በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1 ሺህ 840 ትምህርት ቤቶች መገንባታቸው ተገለጸ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1 ሺህ 840 ትምህርት ቤቶች መገንባታቸው ተገለጸ
በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1 ሺህ 840 ትምህርት ቤቶች መገንባታቸው ተገለጸ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.04.2025
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1 ሺህ 840 ትምህርት ቤቶች መገንባታቸው ተገለጸ

የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ የተገነቡት ትምህርት ቤቶች ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 250 የሚሆነው የቅደመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም 22 ሺህ ለሚደርሱ ትምህርት ቤቶች እድሳት መደረጉን ተናግረዋል። ለትምህርት ቤቶቹ ግንባታ እና ጥገና ሕብረተሰቡ የገንዘብ፣ የዓይነት እና የጉልበት ድጋፍ እንዳደረገ መናገራቸውንም የሀገር ውስጥ የዜና ማሳራጫ ዘግቧል።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0