ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶችን ድጋፍ ጠየቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶችን ድጋፍ ጠየቀች
ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶችን ድጋፍ ጠየቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.04.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶችን ድጋፍ ጠየቀች

በዩኤኢ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን በሀገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ግንኙነት ዳይሬክተር እና የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ ተወካይ ከሆኑት ቱራዬያ አልሃሺሚ ጋር ተወያያተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የባንኩ አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር የሆነችው የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ለአባልነት ጥያቄው ድጋፍ እንድታደርግ ጥያቄ መቅረቡን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

አምባሳደር ዑመር ኢትዮጵያ የባንኩ አባል ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት እና የአዲሱ ልማት ባንክ አባል ለመሆን በሚያስችሏት ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የባንኩ ተወካይ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ ዩኤኢ ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል፡፡

የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች እ.አ.አ ጥቅምት 04፣ 2021 የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክን ተቀላቅላለች፡፡

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0