ሶማሊያ ከአሥርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የመራጮች ምዝገባ ልታካሂድ መሆኑ ተነገረ
15:42 14.04.2025 (የተሻሻለ: 16:04 14.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሶማሊያ ከአሥርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የመራጮች ምዝገባ ልታካሂድ መሆኑ ተነገረ
ሰኔ ላይ ለሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በነገው እለት ይጀመራል።
የሞቃዲሾ ነዋሪዎች ከ50 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጽ ለመስጠት ይመዘገባሉ ሲሉ የምርጫ ኮሚሽን ሰብሳቢው አብዲካሪም አህመድ ሀሰን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ ሶማሊያን ከባህላዊው የጎሳ-ተኮር የምርጫ ስርዓት ለማላቀቅ ቃል ገብተዋል። ካቢኔቸው በ2026 ለሚካሄደው ምርጫ የአንድ ሰው፣ አንድ ድምጽ የምርጫ ስርዓትን አጽድቋል፡፡
በሀገሪቱ እ.አ.አ በ2022 የተካሄደው ምርጫ የጎሳ ስርዓትን መሠረት ያደረገ ነበር። ሶማሊያ ከአውሮፓውያኑ 1967 ወዲህ ቀጥተኛ ምርጫ አካሂዳ አታውቅም።