ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 215 ሺህ ቶን ማር አመረተች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 215 ሺህ ቶን ማር አመረተች
ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 215 ሺህ ቶን ማር አመረተች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.04.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 215 ሺህ ቶን ማር አመረተች

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 210 ሺህ ቶን ማር ለማምረት እቅድ ተይዞ እንደነበር ያስታወሱት የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ ከእቅድ በላይ አፈጻጸም መመዝገቡን ገልጸዋል።

ለተገኘው ከፍተኛ ምርት ባህላዊ የንብ ቀፎዎችን ወደ ዘመናዊ ቀፎ የመለወጥ ሥራ በስፋት መሠራቱ ምክንያት እንደሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ከአንድ ባህላዊ ቀፎ ከ10 ኪ.ግ የማይበልጥ ምርት ይገኝ እንደነበርና ከዘመናዊ ቀፎ ግን ከ35 ኪ.ግ በላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1.9 ሚሊዮን ዘመናዊ እና የሽግግር የንብ ቀፎ ለሕብረተሰቡ መሰራጨቱን ሚኒስትር ዴኤታውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0