የሱዳን አትሌቲክስ ፈርጥ አዶ አቡበከር ካኪ የሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ሰለባ ሆነ
13:02 14.04.2025 (የተሻሻለ: 13:24 14.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሱዳን አትሌቲክስ ፈርጥ አዶ አቡበከር ካኪ የሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ሰለባ ሆነ
ካኪ የጃንጃዊድ ሚሊሺያዎች ኤል-ፋሽር በሚገኘው የመኖሪያ ቤቱ ባደረሱት ጥቃት እንደተገደለና የቤተሰብ አባላቱም ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘግቧል።
ሚዲያዎች ካኪ የሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ ወደ ሆነችው ኤል-ፋሽር በሰብዓዊ ቀውሱ ምክንያት ቤተሰቦቸን ለማገዝ እንደተመለሰ ዘግበዋል። ሯጩ ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በሀገር ወዳድነቱ እና ለሰላም በመሟገት ይታወቃል።
ሁለት ጊዜ የስምንት መቶ ሜትር የወጣቶች የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናው በኦሎምፒክ እና በዓለም ሻምፒዮና ሱዳንን ወክሏል።
የካኪን ግድያ ተከትሎ የጃንጂዊድ ሚሊሻዎች በዳርፉር ሲቪሎች ላይ በሚያደርሱት ጥቃት ዙሪያ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ ቀርቧል።