ሶማሊላንድ ለአሜሪካ ስትራቴጂክ ቦታዎችን በመስጠት ከአሜሪካ እውቅና ለማግኘት እንደምትፈልግ ተገለጸ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሶማሊላንድ ለአሜሪካ ስትራቴጂክ ቦታዎችን በመስጠት ከአሜሪካ እውቅና ለማግኘት እንደምትፈልግ ተገለጸ
ሶማሊላንድ ለአሜሪካ ስትራቴጂክ ቦታዎችን በመስጠት ከአሜሪካ እውቅና ለማግኘት እንደምትፈልግ ተገለጸ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.04.2025
ሰብስክራይብ

ሶማሊላንድ ለአሜሪካ ስትራቴጂክ ቦታዎችን በመስጠት ከአሜሪካ እውቅና ለማግኘት እንደምትፈልግ ተገለጸ

ነጻነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ ለረዥም ዓመታት በሚቆይ ስምምነት የበርበራ ወደብ እና በሶቪየት ህብረት የተሠራውን 4.1 ኪሎ ሜትር የአውሮፕላን ማረፊያ በመስጠት ከአሜሪካ ጋር በመደራደር ላይ እንደምትገኝ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ስምምነቱ በኤደን ባህረ ሰላጤ 800 ኪሎ ሜትር የባህር ዳርቻ ላይ የአሜሪካ የጦር ሰፈርን መመስረት ሊያካትት እንደሚችል በዘገባው ተመልክቷል።

የሶማሊላንድ መሪ አብዲራማን ሞሐመድ አብዱላሂ ድርድሩን ለማዳበር በቅርቡ ዋሽንግተንን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ስምምነቱ አሜሪካ ወሳኝ በሆነው የመርከብ መስመር እና የግጭት ቀጣናዎች አቅራቢያ ስትራቴጂካዊ ቦታ እንድታገኝ ያስቸላታል ተብሏል፡፡ ሶማሊላንድ ከባለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮ የአሜሪካን የጦር ሰፈር ለማስተናገድ ዝግጁ እንደሆነች ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት በበኩሉ ዋሽንግተን ለሶማሊላንድ እና ፑንትላንድ ራስ ገዝ ግዛቶች እውቅና እንዳትሰጥ በኤደን ባህረ ሰላጤ ወደቦች ላይ “ልዩ የኦፕሬሽን ቁጥጥር” እንድትወስድ የድርድር ሃሳብ ማቅረቡ ተዘግቧል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0