ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በርካታ ቁልፍ የትብብር ስምምነቶችን ተፈራረሙ
10:47 14.04.2025 (የተሻሻለ: 11:04 14.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በርካታ ቁልፍ የትብብር ስምምነቶችን ተፈራረሙ
ስምምነቶቹ የሀገራቱን የቆየ የዳፕሎማሲ ግንኙነት የሚያጠናክሩ መሆናቸውን በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢትዮ-አልጄሪያ አምስተኛ ዙር የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ውይይት ላይ ተጠቅሷል።
ሁለቱ ሀገራት በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በሳይንስና አካዳሚ፣ በኃይልና ማዕድን፣ በጋራ የቢዝነስ ምክር ቤት፣ በግብርና፣ በፈጠራ፣ ስፔስ ሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ በጤና እና ፋርማሱቲካል ኢንዱስትሪ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
እንዲሁም በባህልና ስፖርት መስኮች የኢትዮ-አልጄሪያን ታሪካዊ የዲፕሎማሲ ትብብር ለማጠናከር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማሕበራዊ ትሥሥር ገፁ አስነበቧል።
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ