የቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዜንኮቭ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
18:53 13.04.2025 (የተሻሻለ: 19:04 13.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዜንኮቭ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የቤላሩስ ፕሬስ አገልግሎት አስታውቋል።
ውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግኑኝነት በተለይም በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ስላሉ የትብብር እድሎች ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ የፕሬስ አገልግሎቱ ጨምሮ ገልጿል።
ሚኒስትሮቹ በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዩች ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል።
የቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት አመራሮች፣ ሚኒስትሮች እና የንግዱ ማሕበረሰብ ጋር ይወያያሉ ተብሏል።