ኢትዮጵያ ለእንሰሳት ሀብት ልማት ኢንቨስትመንት ከፍተኛ አቅም እንዳላት ባለሙያዋ ተናገሩ
17:16 13.04.2025 (የተሻሻለ: 17:44 13.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለእንሰሳት ሀብት ልማት ኢንቨስትመንት ከፍተኛ አቅም እንዳላት ባለሙያዋ ተናገሩ
በግብርና ሚኒስትር የእንስሳት እና የዓሣ ሀብት ልማት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፅጌሬዳ ፍቃዱ የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን የእንስሳት ሀብት ልማት ኢንዱስትሪ ከፍተኛ አቅም ለመጠቀም ማሻሻያዎችን እያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።
ዘርፉ ከኢንቨስትመንት አኳያ ትርፋማ እንደሆነ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፤ ከጠቅላላ የግብርና ምርት 26 በመቶውን እንደሚሸፍንና ለሥራ ፈጠራ ወሳኝ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የእንስሳት እና የዓሣ ሀብት ልማት የሀገር ውስጥ እና የወጪ ገበያዎችን ለማሳደግ የእንሰሳት ምግብ ምርት እና አቅርቦትን፣ የዘር ጥራትን እና የእንስሳት መጓጓዣን እያሻሻለ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የእንስሳት ሕክምና ዘርፍ ሌላው የኢንቨስትመንት "ዋና መስክ" መሆኑን አመላክተዋል።
"በተለይም የእንስሳት ሕክምና መድሐኒቶች እና ክትባቶች በማምረት እና በማሰራጨት ረገድ ከፍተኛ ዕድሎች አሉ" ብለዋል።
መንግሥት ከታች የተዘረዘሩትን ማበረታቻዎች ለባለሃብቶች እንደሚሠጥም ጠቁመዋል።
🟠 የመሬት አቅርቦት፣
🟠 የግብር እፎይታ፣
🟠 አጠቃላይ የአተገባበር መመሪያ።