ዘጠኝ የአፍሪካ ሀገራት እና ህንድ ታንዛኒያ ውስጥ የጋራ ልምምድ ጀምሩ
16:15 13.04.2025 (የተሻሻለ: 18:44 13.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዘጠኝ የአፍሪካ ሀገራት እና ህንድ ታንዛኒያ ውስጥ የጋራ ልምምድ ጀምሩ
የልምምዱ የመጀመሪያ የባሕር ዳርቻ ምዕራፍ የጋራ ልምምድ፣ የጋራ ዘመቻ እና ስትራቴጂካዊ እቅዶችን መወያየት እንዲሁም ልምዶችን መለዋወጥ ያካትታል።
የልምምዱ ሁለተኛ ምዕራፍ በባሕር ላይ የሚደረግ ሲሆን ከሚያዚያ 8 እስከ 10 ድረስ ይቆያል። ትኩረቱን የባሕር የፀጥታ ትብብርን ማጠናከር እና የመርከበኞችን ክህሎት ማሳደግ፣ የፍለጋ እና አድን ሥራ እንዲሁም የአነስተኛ ጦር መሳሪያዎች ተኩስ እና የሄሊኮፕተር ኦፕሬሽኖች ላይ ያደርጋል።
ተሳታፊ ሀገራት የሚከተሉትን ያካትታል፦
ኮሞሮስ፣
ጅቡቲ፣
ኬንያ፣
ማዳጋስካር፣
ሞሪሸስ፣
ሞዛምቢክ፣
ሲሼልስ፣
ደቡብ አፍሪካ።
የህንድ-አፍሪካ ቁልፍ የባሕር ልምምድ ለጋራ ተግዳሮቶች በጋራ መፍትሄ ማምጣት፣ ትብብርን ማሳደግ፣ በአጋር የባሕር ኃይሎች መካከል የጋራ ዘመቻዎችን ማመቻቸት እና በህንድ እና አፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከርን ያነገበ ነው።