በአፍሪካ የኤምፖክስ በሽታ ስርጭት እንደተባባሠ ተገለፀ

ሰብስክራይብ

በአፍሪካ የኤምፖክስ በሽታ ስርጭት እንደተባባሠ ተገለፀ

በአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ እና ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) ሪፖርት መሠረት እ.አ.አ. በ2025 የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራቶች በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2024 አጋማሽ የበለጠ ነው።

በአፍሪካ ሲዲሲ የኤምፖክስ ምክትል የክስተቶች አስተዳዳሪ ያፕ ቦም "በበሽታው የተጠረጠሩ እና መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን እያየን ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በአፍሪካ ኤምፖክስ በሽታ ጭማሬ ዙሪያ ቁልፍ መረጃዎች፦

▪በ2025 ሶስት ወራት ውስጥ ከ39 ሺህ 800 በላይ ሰዎች በበሽታው ተጠርጥረዋል።

▪በ2025 ሶስት ወራት ውስጥ ከ9 ሺህ በላይ በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

▪ባለፈው ሳምንት ከ2 ሺህ 760 በላይ አዳዲስ የተጠረጠሩ ሰዎች ተለይተዋል።

በሳምንቱ ከ500 በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ 13 ተዛማጅ ሞት ተመዝግቧል።

እንደ ባለሥልጣኑ ገለጻ ኡጋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለፈው ሳምንት በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች 94 በመቶውን መዝግበዋል።

ከ2024 መጀመሪያ ጀምሮ 22 የአፍሪካ ሀገራት 117 ሺህ 678 የኤምፖክስ ኬዞችን፣ 26 ሺህ 927 የተረጋገጡ ኬዞችን እና ከ1 ሺህ 700 በላይ ተዛማች ሞቶችን መመዝገባቸውን አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0