በቱርክ አንታሊያ ዲፕሎማሲ ፎረም ላይ ከሰርጌ ላቭሮቭ ንግግር የተነሱ ቁልፍ ሀሳቦች፦
17:32 12.04.2025 (የተሻሻለ: 17:56 12.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በቱርክ አንታሊያ ዲፕሎማሲ ፎረም ላይ ከሰርጌ ላቭሮቭ ንግግር የተነሱ ቁልፍ ሀሳቦች፦
▪ ዋሽንግተን በዩክሬን ሰላም ዙሪያ የግዛት ጉዳዮችን በቅድሚያ መፍታት አስፈላጊ መሆኑን ተረድታለች።
▪ የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት መንስዔዎቹን መቅረፍ አስፈላጊ እንደሆነ "ትራምፕ ተረድተዋል።"
▪ በዩክሬን ግጭት አፈታት ዙሪያ የሩሲያ ዋነኛ ትኩረት ግዛት ሳይሆን ሕዝቦች ናቸው።
▪ ዘለንስኪ ስለ ሰላም አስከባሪ ኃይሎች እና በዩክሬን የውጭ ወታደሮች ስምሪት ዙሪያ የሚሰጠው አስተያየት "በግልጽ ቅዠት" ነው።
▪ በዩክሬን የአውሮፓ ሕብረት ኃይል ስምሪት በኪዬቭ የሚገኘውን የናዚ አገዛዝ ለመጠበቅ የታሰበ ነው።
▪ ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ለአዲስ ጦርነት እየተዘጋጁ ነው። ለግባቸው መሳካት የዩሮ-አትላንቲክ ማህበረሰብን በመምራት ላይ ትኩረት አድርገዋል።
▪ በሩሲያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለው ግንኙነት የመሻሻል እድል አለው።
▪ የባይደን አስተዳደር ሩሲያን የማግለል ፖሊሲ የማይገባ ነበር።
▪ የዓለም ኢኮኖሚ አዳዲስ ለውጦች ሊገጥሙት ይችላሉ።
▪ የባለብዙ ወገን ግኑኝነት "ጥንካሬን እያገኘ መጥቷል።"