ኢትዮጵያ እና የሩሲያው ፔትሮቨስኪ የሳይንስ እና የሥነ-ጥበብ አካዳሚ በባህል እና በሌሎች ዘርፎች አብረው ለመሥራት ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ እና የሩሲያው ፔትሮቨስኪ የሳይንስ እና የሥነ-ጥበብ አካዳሚ በባህል እና በሌሎች ዘርፎች አብረው ለመሥራት ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና የሩሲያው ፔትሮቨስኪ የሳይንስ እና የሥነ-ጥበብ አካዳሚ በባህል እና በሌሎች ዘርፎች አብረው ለመሥራት ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.04.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና የሩሲያው ፔትሮቨስኪ የሳይንስ እና የሥነ-ጥበብ አካዳሚ በባህል እና በሌሎች ዘርፎች አብረው ለመሥራት ተስማሙ

በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ከፔትሮቭስኪ የሳይንስ እና የሥነ-ጥበብ አካዳሚ ተወካይ ሰርጌ ቼስኖኮቭ ጋር በትብብር ሊሠሩባቸው በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ አደገኛ ንጥረ ነገሮች ማስወገድን በተመለከተ እና በቴሌ ህክምና በጋራ ሊሠሩ እንደሚችሉ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

በተጨማሪም በኦንላይን የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት መጀመር ስለሚቻልበት መንገድ መክረዋል።

አምባሳደር ገነት ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች መሥራት እንደምትሻም በውይይቱ ወቅት መግለጻቸውን ሞስኮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0