የሩሲያና አሜሪካ የዲፕሎማሲ ተልዕኮዎችን ሥራ ዳግም ማስጀመርን በተመለከተ የተደረገው ውይይት በአዎንታዊ መንፈስ እንደተጠናቀቀ በአሜሪካ የሩሲያ አምባሳደር አሌክሳንደር ዳርቺዬቭ ተናገሩ
20:27 10.04.2025 (የተሻሻለ: 20:44 10.04.2025)
ሰብስክራይብ
የሩሲያና አሜሪካ የዲፕሎማሲ ተልዕኮዎችን ሥራ ዳግም ማስጀመርን በተመለከተ የተደረገው ውይይት በአዎንታዊ መንፈስ እንደተጠናቀቀ በአሜሪካ የሩሲያ አምባሳደር አሌክሳንደር ዳርቺዬቭ ተናገሩ
በኢስታንቡል በተደረገው ውይይት ዙሪያ የሩሲያው ዲፕሎማት የሰጡት ተጨማሪ መግለጫዎች፦
▪የልዑካን ቡድኑ መሪዎች የቀድሞው የአሜሪካ አስተዳደር አዋኪ ጉዳዮች መቀረፍ እንዳለባቸው አመልክተዋል።
▪ሁለቱ ወገኖች የዲፕሎማቶችን እንቅስቃሴ ለማቃለል በሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች ላይ ተስማምተዋል።
▪ሩሲያ በአሜሪካ የተወረሰባትን የዲፕሎማሲ ንብረት ማስመለስን ቅድሚያ እንደምትሰጥና ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።
▪ዲፕሎማቶቹ ለዲፕሎማሲ ተልዕኮዎች ያልተቋረጠ የባንክ አገልግሎት አቅርቦት ስምምነትን የተመለከተ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።
▪የሩሲያና አሜሪካ ቀጣይ ዙር ምክክር የሚካሄድበትን ቀን ለመወሰን ዝርዝር እቅድ እየወጣ ነው።