አሜሪካ በኢራን ላይ የምትወስደው ወታደራዊ እርምጃ የቀጣናውን ስለም አደጋ ላይ ይጥላል ስትል ቱርክ ገለፀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ በኢራን ላይ የምትወስደው ወታደራዊ እርምጃ የቀጣናውን ስለም አደጋ ላይ ይጥላል ስትል ቱርክ ገለፀች
አሜሪካ በኢራን ላይ የምትወስደው ወታደራዊ እርምጃ የቀጣናውን ስለም አደጋ ላይ ይጥላል ስትል ቱርክ ገለፀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.04.2025
ሰብስክራይብ

አሜሪካ በኢራን ላይ የምትወስደው ወታደራዊ እርምጃ የቀጣናውን ስለም አደጋ ላይ ይጥላል ስትል ቱርክ ገለፀች

የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን አሜሪካ እና ኢራን በተቻለ ፍጥነት የፊት ለፊት ንግግር በማድረግ አለመግባባታቸውን ያለ ኃይል መፍታት ይችላሉ ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ "ኢራን የኒውክሌር አቅም አላት፤ የጦር መሳሪያው ግን የላትም። ትራምፕ ለድርድር ዝግጁ ናቸው ብዬ አስባለሁ" ሲሉ ሃሳባቸውን ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ነገሮች የሚያስገድዱ ከሆነ አሜሪካ ለወታደራዊ አማራጭ ዝግጁ መሆኗን እሮብ እለት አስታውቀዋል። "እስራኤል በዚህ ውስጥ በጣም ትሳተፋለች" ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለማምረት ተቃርባለች ሲሉ በተደጋጋሚ ስጋታቸውን ይገልጻሉ። ቴህራን በበኩሏ መሳሪያውን የማምረት እቅዱም እንደሌላት ትናገራለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0