ሱዳን በተመድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሰሰች
19:08 10.04.2025 (የተሻሻለ: 19:34 10.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሱዳን በተመድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሰሰች
የፍትህ ሚኒስትሩ ሙአውያ ዑስማን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (አይሲጄ) ቀርበው ባደረጉት ንግግር "ከምዕራብ ዳርፉር ክልል የመጡ አረቦች ናቸው ተብሎ የሚታሰቡት ፈጣኖ ደራሽ ኃይሎች በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ታግዘው በማሳሊት ብሄረሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀሙ ነው" ብለዋል።
ሚኒስትሩ ፈጣኖ ደራሸ ኃይሉ እና አጋሮቹ ባለፈው ዓመት በምዕራብ ዳርፉር ከ10 ሺህ እስከ 15 ሺህ የሚደርሱ ማሳሊቶችን መግደላቸውን ተናግረዋል። ዑስማን አክለውም አማፂያኖቹ የሰሜን ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ የሆነችውን ኤል ፋሸርን የሚቆጣጠሩ ከሆነ ተመሳሳይ እልቂት ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
እንደ ባለስልጣን ገለጻ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች
ለፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በምትሰጠው የሎጂስቲክስ እና ሌሎችም ድጋፎች አየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት እያፋፋመች ነው።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በበኩሏ የሱዳንን ክስ አስተባብላለች። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከፍተኛ ባለስልጣን ሪም ኬታይት የአይሲጄ ችሎት ከመጀመሩ በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት ክሱን "የፌዝ እና መሠረተ ቢስ የህዝብ ግንኙነት መኩራ" ብለውታል።
ሱዳን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የተመድ የዘር ማጥፋት ስምምነት ግዴታዎቿን ጥሳለች በማለት በመጋቢት ወር ነበር በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ክስ የመሠረተችው።