ኢትዮጵያ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠረች
16:56 10.04.2025 (የተሻሻለ: 17:14 10.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠረች
ይሄ የተገለፀው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው።
ሪፖርቱን ያቀረቡት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በግብርና፣ በአገልግሎት እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በሀገር ውስጥና ውጭ ሀገራት ዜጎችን በማሰልጠን እና በማብቃት ወደ ሥራ ማሠማራት እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ሁሉንም አካባቢዎች ታሳቢ ያደረገ ለዜጎች ፍታሃዊ የሆነ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደሚገባ እና ዜጎች ሰብዓዊ መብታቸውና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ውጭ ሀገራት መሠማራት እንዳለባቸው አስረግጠዋል፡፡
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
