አፍሬክሲምባንክ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆነ ገለፀ
15:26 10.04.2025 (የተሻሻለ: 15:34 10.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፍሬክሲምባንክ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆነ ገለፀ
የአፍሬክሲምባንክ የቁጥጥር ዳይሬክተር ኢድሪሳ ዲዮፕ ኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ገበያና ለአህጉሪቱ ዕድገት ወሳኝ ሀገር ነች ብለዋል።
ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ አሁን በሥራ ላይ ያዋለቻቸው ሕጎች በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምልከታ ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳሳደሩ ተናግረዋል፡፡
አፍሬክሲምባንክ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሀገር ውስጥ ንግዶችንና የፋይናንስ ተቋማትን ሲደግፍ እንደነበርም አስታውሰዋል።
ባንኩ የኢትዮጵያን ንግድ ለማጠናከር እና ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማትና ኩባንያዎች ጋር በመተባበር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ከመንግሥት ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልፀዋል።