"ወደ ዩክሬን የሚላኩ የምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎች መዳረሻቸው አፍሪካ ነው"
14:28 10.04.2025 (የተሻሻለ: 14:44 10.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ወደ ዩክሬን የሚላኩ የምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎች መዳረሻቸው አፍሪካ ነው"
ይህ እየሆነ ያለው የሩሲያ አሰልጣኞች ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ሽብርተኝነት እንድትዋጋ ድጋፍ እያደረገች ባለበት ወቅት ነው ሲሉ የዓለም አቀፍ ደህንነት መኮንኖች ማሕበረሰብ ዳይሬክተር አሌክሳንደር ኢቫኖቭ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የሩሲያ ወታደራዊ አስልጣኞች የሀገሪቱን "ሰላም እና ፀጥታን ለመመለስ ትልቅ ሥራ" እንደሠሩም ኃላፊው አስታውቀዋል። ይህም ሕዝቡ ወደ ቄዬው እንዲመለስ፣ የመሠረተ ልማት መልሶ ግንባታ እና የኢኮኖሚ መነቃቃት ማምጣቱን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ጥረቱ የማዕከላዊ አፍሪካ ሕዝብ በሀገሪቱ መጪ ዘመን እምነት እንዲኖረው አድርጓል ሲሉ ኢቫኖቭ ገልጸዋል።
"ዛሬ 95% የሚሆነው የሪፐብሊኩ ግዛት በትክክለኛው እና ሕጋዊው መንግሥት ቁጥጥር ሥር ነው። የአሰልጣኞቹ ሥራ ለአፍታም ቢሆን አይቆምም" ሲሉ አስተያየታቸውን አጠቃለዋል።
@sputnik_ethiopia