ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በቦቴ የሚገባው ነዳጅ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ በባቡር ይጓጓዛል ተባለ
11:33 10.04.2025 (የተሻሻለ: 12:04 10.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በቦቴ የሚገባው ነዳጅ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ በባቡር ይጓጓዛል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ በቦቴ የሚገባው ነዳጅ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ በባቡር ይጓጓዛል ተባለ
በባቡር መጓጓዙ የነዳጅ ዋጋ ላይ ቅናሽ ቅናሽ ሊያመጣ እንደሚችል የኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር አክሲዮን ማኅበርን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
በባቡሩ በቀን እስከ አስር ጊዜ በመመላለስ በዓመት 4.2 ሚሊዮን ቶን ነዳጅ ለማመማለስ የታቀቀደ ሲሆን ይህ የነዳጅ አቅርቦት ችግርን ከመቅረፉም በላይ የነዳጅ ማጓጓዣ ጊዜን ይቀንሳል ተብሎ ታምኗል።
ከአዋሽ እስከ ጂቡቲ ድረስ ያለው የባቡር መስመር ዝርጋታ ሙሉ ሙሉ ሲጠናቀቅ በመጪው ዓመት አገልግሎቱ እንደሚጀመር ተጠቁሟል።
የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር መስመር ፍጥነት በሰዓት 37 ኪ.ሜ ከነበረው የጉዞ ፍጥነት ወደ 60 ኪ.ሜ እንዳደገ መገለፁ ይታወሳል።
@sputnik_ethiopia