የአፍሪካ ሕብረት ከአውሮፓ ሕብረት ጋር በሚያደርገው ግንኙነት በካሳ ክፍያ ዙሪያ ጫና ማሳደር አለበት ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኃላፊ ተናገሩ
18:53 09.04.2025 (የተሻሻለ: 19:14 09.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአፍሪካ ሕብረት ከአውሮፓ ሕብረት ጋር በሚያደርገው ግንኙነት በካሳ ክፍያ ዙሪያ ጫና ማሳደር አለበት ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኃላፊ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሕብረት ከአውሮፓ ሕብረት ጋር በሚያደርገው ግንኙነት በካሳ ክፍያ ዙሪያ ጫና ማሳደር አለበት ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኃላፊ ተናገሩ
በአውሮፓና በሌሎችም ቦታዎች የቀኝ ዘመም እንቅስቃሴ እየጨመረ ቢመጣም አፍሪካ ለቅኝ ግዛትና ለአትላንቲክ የባሪያ ንግድ ካሳ መጠየቅ አለባት ሲሉ በአፍሪካ ሕብረት የዲያስፖራ ጉዳዮች ክፍል ኃላፊ አንጄላ ናአ አፎሌ ኦዳይ ለእንግሊዝ ሚዲያ ተናግረዋል።
"የተለያዩ አመቺ ያልሆኑ ጉዳዮች ቢኖሩም የካሳ ክፍያን ለማንሳት ከዚህ የተሻለ ጊዜ የለም" ሲሉ ኃላፊው አስረግጠዋል።
በየካቲት ወር የተካሄደው 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ የማካካሻ ፍትሕ እና በአህጉሪቱ ላይ የተፈፀመውን ዘር ተኮር አድልዎ ማከም ላይ ያተኮረ ነበር። ግቡን ለማሳካት ሕብረቱ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ማሳደር እና በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ሕጋዊ እርምጃ መውሰድን እንደ አንደ ስትራቴጂ እንደሚመለከተው ቀደም ሲል ገልጿል።
በዚህ ረገድ በአፍሪካ ሕብረት እና ካሪቢያን እንዲሁም የአውሮፓ ሕብረት መካከል የሚደረጉ ትብብሮች ካሳን በተመለከተ የተቀናጀ ግንባር መፍጠሪያ መንገዶች እንደሆኑ ኃላፊው ጠቁመዋል።
በሰው ሰራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
@sputnik_ethiopia