ናሚቢያ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የንግድ ደንቦችን እንድታከብር አሳሰበች

ሰብስክራይብ

ናሚቢያ አሜሪካ ዓለም አቀፍ የንግድ ደንቦችን እንድታከብር አሳሰበች

የናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰልማ አሺፓላ-ሙሳቪ ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር "ይህ የአንድ ወገን እርምጃ ግልጽነትን እና አባላት በሌሎች የዓለም ንግድ ድርጅት አባላት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ውሳኔዎችን ከማድረጋቸው በፊት በቅድሚያ ማሳወቅ እንዳለባቸው የሚያስቀምጠውን የባለብዙ ወገን የንግድ ስርዓት መርህ ይቃረናል" ብለዋል።

ዲፕሎማቷ እሮብ እለት ተግባራዊ የሚሆነው 21% የአሜሪካ ቀረጥ እንደ አሳ፣ ማዕድናት እና ስጋ ያሉ ወሳኝ የናሚቢያ ምርቶች ላይ ሊጣል እንደሚችል ጠቁመው ይህም ወደ አሜሪካ የሚላኩ ምርቶችን እንደሚቀንስ ተናግረዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ያነሷቸው ተጨማሪ አስተያየቶች፡-

አዲሱ የአሜሪካ ቀረጥ ዋሽንግተን በአፍሪካ እድገትና ዕድል ድንጋጌ (አጎዋ) እና በዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት ሥር የገባችውን ኃላፊነት የሚሸረሽር ነው።

ናሚቢያ "አሜሪካ ቅድሚያ" ፖሊሲ በንግድ ስምምነቶች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ትከታተላለች።

የአጎዋን ጥቅሞች ለመገምገም መንግሥት ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ቀረጡ ዙሪያ ይወያያል።

ዊንድሆክ በአሜሪካ ቀረጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት የሚሰጡትን ምላሽ ትከታተላለች።

የናሚቢያ መንግሥት የሚሰጠው የትኛውም ምላሽ በመረጃ ላይ የተመሠረተ ይሆናል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0