በአፍሪካ ጥንታዊ ፓርክ ውስጥ የተከሰተ የአንትራክስ ወረርሽኝ ከሃምሳ በላይ ጉማሬዎችን ገደለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአፍሪካ ጥንታዊ ፓርክ ውስጥ የተከሰተ የአንትራክስ ወረርሽኝ ከሃምሳ በላይ ጉማሬዎችን ገደለ
በአፍሪካ ጥንታዊ ፓርክ ውስጥ የተከሰተ የአንትራክስ ወረርሽኝ ከሃምሳ በላይ ጉማሬዎችን ገደለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.04.2025
ሰብስክራይብ

በአፍሪካ ጥንታዊ ፓርክ ውስጥ የተከሰተ የአንትራክስ ወረርሽኝ ከሃምሳ በላይ ጉማሬዎችን ገደለ

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቪሩንጋ ፓርክ ዳይሬክተር አማኑኤል ዴ ሜሮዴ ትክክለኛው ምክንያት እስካሁን ባይታወቅም የአንትራክስ ወረርሽኝ መሆኑን ለአንድ የምዕራባውያን የዜና ወኪል አረጋግጠዋል።

የጉማሬዎቹ ሞት ከ1999 ጀምሮ ጥቂት መቶ የነበርውን የጉማሬ ቁጥር ወደ 1 ሺህ 200 ለማሳደግ በፓርኩ የተደረገውን ጥረት በእጅጉ የሚያደናቅፍ ነው ተብሏል።

ባለሥልጣናት ነዋሪዎች ውሃ ከመጠቀማቸው በፊት እንዲያፈሉ እና ከዱር እንስሳት እንዲርቁ አስጠንቅቀዋል። ሪፖርቱ በተጨማሪም አስከሬኖችን ለማስወገድ እና ለመቅበር ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም በመዳረሻ እና የመሳሪያ እጥረት እክል ምክንያት የሎጂስቲክ ችግሮች አሁንም እንዳሉ ገልጿል።

ከ25 በላይ የጉማሬ አስከሬኖች በኤድዋርድ ሀይቅ ውስጥ እንዳሉ የሚገልጹ ዘገባዎች ተጨማሪ ብክለት ይፈጠራል የሚል ስጋት ፈጥረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0