ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 4.5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘቷን መንግሥት ገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 4
ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 4 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.04.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 4.5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘቷን መንግሥት ገለፀ

ይህ ገቢ በሀገሪቱ ወጪ ንግድ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑን፤ የበጀት ዓመቱን የ9 ወራት አፈጻጸም የገመገሙበት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ አስታውቀዋል።

በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ክትትል ከሚደረግባቸው የወጪ ንግድ ምርቶች ከ595 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱን የገለጹ ሲሆን ይህም ከዕቅዱ 98.2% በላይ ነው ብለዋል።

በኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፊቃድ ለ2.6 ሚሊዮን ተገልጋዮች አገልግሎት መሰጠቱንም ተናግረዋል። እንዲሁም የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ በበጀት ዓመቱ 9 ወራት 374 ተጨማሪ የሰንበት ገበያዎችን በማቋቁም 1 ሺህ 476 ሰንበት ገበያዎች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ በቀጣይ ዓመት በየካቲት ወር የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0