የተዘርፉ የራስ ደስታ ዳምጠው ቅርሶችን ለማስመለስ እንቅስቃሴ ተጀመረ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየተዘርፉ የራስ ደስታ ዳምጠው ቅርሶችን ለማስመለስ እንቅስቃሴ ተጀመረ
የተዘርፉ የራስ ደስታ ዳምጠው ቅርሶችን ለማስመለስ እንቅስቃሴ ተጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.04.2025
ሰብስክራይብ

የተዘርፉ የራስ ደስታ ዳምጠው ቅርሶችን ለማስመለስ እንቅስቃሴ ተጀመረ

በጣሊያን ወረራ ወቅት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በመዋደቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጀግና የሆኑት የራስ ደስታ ዳምጠው የተዘረፉ ቁሶችን ለማስመለስ መንግሥትና የልጅ ልጆቻቸው እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡

ራስ ደስታ ዳምጠው በፈረንጆቹ 1929 በጣሊያን ፋሺስቶች ከተገደሉ በኋላ ሰይፍ እና ካባቸው ተዘርፈው ወደ ጣሊያን ተወስደዋል።

የራስ ደስታ ዳምጠው ሰይፍና ካባ ባለፈው ወር በጣሊያን ብሬሻ ከተማ በሚገኘው የጣሊያን ጨረታ ቤት ካፒቶሊየም አርት ድረ-ገጽ ላይ ለጨረታ ቀርበው እንደነበር ዘገባዎች ጠቁመዋል።

ጨረታው መጋቢት 30 ሊካሄድ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ሽያጩ እንዲቆምና የሚጠይቅ ደብዳቤ መጻፉን ተከትሎ ተሰርዟል። የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣኑ ለጨረታ የቀረቡት ሰይፍ እና ካባ ወደ ኢትዮጵያ አንዲመለሱም ጠይቋል፡፡

ኢትዮጵያ በጣሊያን እና እንግሊዝ የተዘረፉ በርካታ ቅርሶቿ አሁንም በውጭ ሀገራት እንደሚገኙ ይታመናል፡፡

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0