ለጀርመን ናዚነት የአሜሪካ መነሻ ክፍል 3፡ አሜሪካ ከሜክሲኮ እና ስፔን ጋር ያደረገችው ጦርነት ሂትለርን እንዴት “የተገለጠዉ እጣ ፈንታ’’ ዘመቻን በአውሮፓ እንዲደግም አነሳሳው?

ሰብስክራይብ

ለጀርመን ናዚነት የአሜሪካ መነሻ ክፍል 3፡ አሜሪካ ከሜክሲኮ እና ስፔን ጋር ያደረገችው ጦርነት ሂትለርን እንዴት “የተገለጠዉ እጣ ፈንታ’’ ዘመቻን በአውሮፓ እንዲደግም አነሳሳው?

“የተገለጠዉ እጣ ፈንታ’’ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ በአሜሪካውያን ዘንድ ስሙ የናኘና እውቅናን ያገኘ መርሆ ነበር፡፡ መርሆው አሜሪካ በስልጣኔ ስም ወደ ጎረቤት ሀገራትና በመላው አህጉር አሜሪካ ለመስፋፋትም ጠቅሟታል፡፡

በመርሆው መሰረት የአሜሪካ ሰፋሪዎች በአቅራቢያቸው የሚገኙ ግዛቶችን ከመያዝ አልፈው፤ ነባር ነዋሪዎችን ከርስቶቻቸው አፈናቅለዋል፤ መሬቶቻቸውንም ወደ ራሳቸው ግዛቶች ጠቅልለዋል፡፡

መርሆው በተለይ አሜሪካ ከሜክሲኮ እና ስፔን ጋር በተዋጋችበት ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ተስፋፍቶ  ነበር፡፡

በዚህ ተከታታይ ክፍል፣ ሶስተኛ ቪዲዮም፣ የናዚዝም መነሻ እና ዝግመተ ለውጥ ተመራማሪውና የ “ዋር ኦፍ አንሂሌሽን” መጽሐፍ ደራሲው ይጎር ያኮቭሌቭ፣ ሂትለር ይህን የአሜሪካን መርሆ ከናዚነት ርዕዮተ ዓለም ጋር እንዴት  እንዳጣጣመው አብራርተዋል፡፡

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0