ሃማስ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ከአፍሪካ ህብረት አዳራሽ መባራራቸውን አወደሰ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሃማስ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ከአፍሪካ ህብረት አዳራሽ መባራራቸውን አወደሰ
ሃማስ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ከአፍሪካ ህብረት አዳራሽ መባራራቸውን አወደሰ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.04.2025
ሰብስክራይብ

ሃማስ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ከአፍሪካ ህብረት አዳራሽ መባራራቸውን አወደሰ

ንቅናቄው አክሎም እስራኤል በጋዛ የምትወስደው እርምጃ ከሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ጋር የሚነጻጸር ነው ብሏል።

"ሃማስ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት በታሰበበት ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ሕብረት የጽዮናዊው (እስራኤል) አምባሳደር እንዲባረሩ በማድረግ ያሳየውን ጠንካራ አቋም በደስታ ይቀበላል" ሲል የፍልስጤሙ ንቅናቄ አስታውቋል።

አምባሳደር አቭርሃም ነጉሴ በርካታ አባል ሀገራት በጉባኤው ላይ መገኘታቸውን መቃወማቸውን ተከትሎ ከአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ መባረራቸው ይታወሳል።

"የጽዮናዊው ወራሪ አካል አረመኔያዊ ሠራዊቱ በጋዛ ሰርጥ በሚገኙ ፍልስጤማውያን ላይ አስከፊና ተሰምቶ የማይታወቅ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመ ባለበት ወቅት የዘር ማጥፋት ወንጀልን በሚመለከት ጉባኤ ላይ ተወካዩን በመላክ እብሪተኝነቱ ከፈተኛ ደረጃ እንደደረሠ አሳይቷል" ሲል ሃማስ አክሎ ገልጿል።

ንቅናቄው ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እስራኤልን እንዲቃወም እና "እጃቸው በንጹሃን ህጻናትና ሲቪሎች ደም የተጨማለቀ መሪዎቿን ተጠያቂ እንዲያደርግ" ጥሪ አቅርቧል።

በጥር 8 በእስራኤል እና ሃማስ መካከል የተደረሰው ስምምነት በጋዛ የሶስት ዙር የተኩስ አቁም ስምምነትና የታጋጆችን መለቀቅ አስቀምጧል። ሆኖም ስምምነቱን በመጣስ የእስራኤል ኃይሎች ከመጋቢት 11 ጀምሮ ከፍተኛ ጥቃት ማካሄድ ጀምረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0