ሁለተኛው የምስራቅ አፍሪካ ኮሪደር ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
14:35 08.04.2025 (የተሻሻለ: 14:54 08.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሁለተኛው የምስራቅ አፍሪካ ኮሪደር ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
የምስራቅ አፍሪካ ከተሞች ኮሪደር ከአዲስ አበባ እስከ በርበራ ወደብ ድረስ በ940 ኪ.ሜ የንግድ መስመር ውስጥ ያሉ ከተሞችን የሚያገናኝ የኢኮኖሚና የፍልሰት እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ ስትራቴጂካዊ ጥረት ነው፡፡
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የከተማና የመሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ደጀን በምስራቅ አፍሪካ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማሳደግ አረንጓዴ መሠረተ ልማት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኮሪደሩ ልማት ቀጣናዊ ንግድና የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት እየሳበ እንደሆነም በመድረኩ ተገልጿል። ኮሪደሩ የከተማ ማዕከላትን ከጠረፍ የንግድ መናኸሪያዎች ጋር የሚያገናኝ ወሳኝ መስመር እንደሆነና በርበራ፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋን የመሳሰሉ ከተሞች ለቀጣናዊ የንግድ መረብ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ ተብራርቷል።
ምስሎች በስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ የተነሱ ናቸው
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
