የኢትዮጵያ እና የቻይና የሁለትዮሽ ንግድ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 3.55 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሶ እንደነበር ተገለፀ
11:10 08.04.2025 (የተሻሻለ: 11:34 08.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ እና የቻይና የሁለትዮሽ ንግድ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 3.55 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሶ እንደነበር ተገለፀ
በቻይና የጉምሩክ አጠቃላይ አስተዳደር መረጃ መሠረት የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥ ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ17.5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
በቤጂንግ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው እያደገ ለመጣው የሁለቱ ሀገራት የንግድ ግኑኝነት የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
አክለውም ቻይና ትልቋ የኢትዮጵያ የንግድ አጋር እንደሆነች ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ገኑኝነታቸውን የጀመሩበት 55ኛ ዓመት ላይ ይገኛሉ፡፡
@sputnik_ethiopia