የሩዋንዳው መሪ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት ምክንያት ማዕቀብ የጣሉ ሀገራትን አወገዙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩዋንዳው መሪ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት ምክንያት ማዕቀብ የጣሉ ሀገራትን አወገዙ
የሩዋንዳው መሪ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት ምክንያት ማዕቀብ የጣሉ ሀገራትን አወገዙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.04.2025
ሰብስክራይብ

የሩዋንዳው መሪ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት ምክንያት ማዕቀብ የጣሉ ሀገራትን አወገዙ

በሩዋንዳ ላይ ማዕቀብ የሚጥሉ ሀገራት በራሳቸው ችግሮች ላይ ያተኩሩ ሲሉ ፖል ካጋሜ ሀገራቱን በስም ሳይጠቅሱ ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ሕብረት ከምስራቅ ኮንጎ ግጭት ጋር በተያያዘ በርካታ ግለሰቦች ላይ መጋቢት 10 ቀን ማዕቀብ ጥሏል። ከእነዚህም መካከል የሩዋንዳ የመከላከያ ኃይሎች ከፍተኛ መኮንኖች እና የሩዋንዳ ማዕድን፣ ነዳጅ እና ጋዝ ቦርድ ዳይሬክተር ፍራንሲስ ካማንዚ ይገኙበታል።

በምላሹም መሪዎቻቸው በአውሮፓ ሕብረት ማዕቀብ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱባቸው የኤም23 አማጺያን ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለስልጣናት ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ እንደማይሳተፉ ገልጸዋል፡፡

ሩዋንዳ ለኤም23 ቡድን ወታደራዊ ድጋፍ እንደማታደርግ ብትገልጽም፤ ሩዋንዳ የጦር ኃይሎቿን በመላክ ሉዓላዊነቴን እና የግዛት አንድነቴን ጥሳለች ስትል ኮንጎ ትከሳለች። ሩዋንዳ በበኩሏ ከ1994ቱ የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ጋር ግንኙነት ያለው የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ዲሞክራሲያዊ ኃይል በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እንደሚደገፍ ትናገራለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0