በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭርሃም ንጉሴ ከአፍሪካ ሕብረት ዋና መሥሪያ ቤት ተባረሩ
19:57 07.04.2025 (የተሻሻለ: 20:14 07.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭርሃም ንጉሴ ከአፍሪካ ሕብረት ዋና መሥሪያ ቤት ተባረሩ
በዛሬው እለት ተካሂዶ በነበረው የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት 31ኛ ዓመት መታሰቢያ ላይ ተጋብዘው የነበሩት አምባሳደሩ፤ አባል ሀገራት አሻፈረን በማለታቸው ምክንያት ከአፍሪካ ሕብረት ዋና መሥሪያ ቤት መባረራቸውን የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኦረን ማርሞርስቲን የጅቡቲው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ፀረ-እስራኤል የፖለቲካ አካላትን ለማስተናገድ መምረጣቸው በጣም አሳዛኝ ተግባር ነው ብለዋል።
"የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ ይወስዳል" ሲሉም ተናግረዋል።
@sputnik_ethiopia