የዋሊያ አይቤክስ ቁጥርን ለመመለስ እና ለማሣደግ ያለመ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተዘጋጀ
19:38 07.04.2025 (የተሻሻለ: 20:04 07.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የዋሊያ አይቤክስ ቁጥርን ለመመለስ እና ለማሣደግ ያለመ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተዘጋጀ
ዕቅዱ የዋሊያ አይቤክስን ደኅንነት ለመታደግ ያለመ ውይይት በጎንደር ከተማ በተካሄደበት ወቅት ይፋ ሆኗል።
በሺዎች ይቆጠር የነበረው ዋልያ አይቤክስ ወደ 300 ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን በቅርቡ ማስታወቁ ይታወሳል።
ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት ተቀናጅተው በመሥራት የሀገር ምልክት የኾነውን ዋሊያ አይቤክስ ከተጋረጠበት አደጋ እንዲከላከሉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።
@sputnik_ethiopia