አፍሪካ በአሜሪካ ቀረጥ ምክንያት አህጉራዊውን ነፃ የንግድ ቀጣና ማጠናከር አለባት ሲሉ የናይጄሪያ ሚኒስትር ተናገሩ
16:51 07.04.2025 (የተሻሻለ: 17:34 07.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአፍሪካ በአሜሪካ ቀረጥ ምክንያት አህጉራዊውን ነፃ የንግድ ቀጣና ማጠናከር አለባት ሲሉ የናይጄሪያ ሚኒስትር ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አፍሪካ በአሜሪካ ቀረጥ ምክንያት አህጉራዊውን ነፃ የንግድ ቀጣና ማጠናከር አለባት ሲሉ የናይጄሪያ ሚኒስትር ተናገሩ
አዲሱ የአሜሪካ ቀረጥ ወሳኝ የናይጄሪያ ምርቶች በአሜሪካ ገበያ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ሊጎዳ ይችላል ሲሉ የናይጄሪያ የኢንዱስትሪ፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ሚኒስትር ጁሞኬ ኦዱዎሌ ተናግረዋል።
በዚህም ናይጄሪያ የኢኮኖሚዋን የመቋቋም አቅም ለማጠናከር እና የወጪ ንግዷን ማብዛት ትፈልጋልች ሲሉ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
ናይጄሪያ እየጨመረ የመጣውን ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ቀረጥ በመቋቋም የሀገር ውስጥ ንግዶችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እንዲሁም ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና ለማቆየት ፖሊሲዎችን፣ የገንዘብ፣ የመሠረተ ልማት እና ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው ብለዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ናይጄሪያ ወደ አሜሪካ የምትለከው ዓመታዊ ምርት ከ5-6 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነበር። ከዚህ ወስጥ 90 በመቶው የኃይል ዘርፉ እንደሚሸፍነውና አሜሪካ ለናይጄሪያ ወሳኝ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አጋር እንደሆነች ሚኒስትሯ ጨምረው ገልጸዋል።
ምስሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሠራ ነው
@sputnik_ethiopia