የሳህል ሀገራት ወታደራዊ ኢንዱስትሪ ለመመሥረት የሩሲያን እገዛ እንፈልጋለን አሉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሳህል ሀገራት ወታደራዊ ኢንዱስትሪ ለመመሥረት የሩሲያን እገዛ እንፈልጋለን አሉ
የሳህል ሀገራት ወታደራዊ ኢንዱስትሪ ለመመሥረት የሩሲያን እገዛ እንፈልጋለን አሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.04.2025
ሰብስክራይብ

የሳህል ሀገራት ወታደራዊ ኢንዱስትሪ ለመመሥረት የሩሲያን እገዛ እንፈልጋለን አሉ

የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱላዬ ዲዮፕ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት "ከሩሲያ ጋር በዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ደህንነትን በሚመለከቱ በርካታ ጉዳዮች ላይ ትብብር ጀምረናል። ሀገሮቻችን ራሳቸውን ችለው ለመቆም እና ጥገኝነትን ለማስወገድ አቅማቸውን ማጠናከር ይፈልጋሉ" ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም የጦር መሳሪያ ግዥ አስቸኳይ አየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።

የጥምረቱ  ሀገራት "ቴክኖሎጂው እና የተረጋገጠ ልምድ ካላት ሩሲያ፣ ከሩሲያ ኩባንያዎች እና ከሩሲያ መንግሥት ጋር በመተባበር በጥምረቱ ቀጣና ወታደራዊ አቅም መፍጠር እንችላለን" ብለዋል።

እንደ ዲዮፕ ገለጻ ይህ ወታደራዊ መሳሪያዎችን ከውጭ ማስገባትን እንደሚቀንስ እና አዲስ የሥራ እድሎችን እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የማሊ፣ የቡርኪናፋሶ እና የኒጀር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ በቀረበላቸው ግብዣ ሞስኮን ባሳለፍነው ሳምንት ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ የሳህል ሀገራት ጥምረት ከሩሲያ ጋር ያደረገው የመጀመሪያው ምክክር አካል ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን

አዳዲስ ዜናዎች
0