ቦይንግ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ከደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ጋር በተያያዘ ዛሬ በፍትሐብሔር ፍርድ ቤት ፊት ይቆማል
12:17 07.04.2025 (የተሻሻለ: 13:54 07.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቦይንግ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ከደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ጋር በተያያዘ ዛሬ በፍትሐብሔር ፍርድ ቤት ፊት ይቆማል

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቦይንግ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ከደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ጋር በተያያዘ ዛሬ በፍትሐብሔር ፍርድ ቤት ፊት ይቆማል
ከአደጋው ጋር በተገናኛ ለመጀመሪያ ግዜ ለፍትሐብሔር ፍርድ ቤት የሚቀርብ ጉዳይ ይሆናል፡፡
ሁለት ሳምንታት ይፈጃል ተብሎ የሚጠበቀው የቺካጎው ችሎት፤ በዚሁ አደጋ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ያጡ ሁለት ከሳሾችን ያካትታል ተብሎ ነበር።
ነገር ግን ከከሳሾቹ አንዱ እሁድ ከፍርድ ቤት ውጭ በተደረገ ስምምነት ጉዳያቸው እንደተፈታ አንድ የፍርድ ቤት ምንጭን ጠቅሶ የምእራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
ሌላ የመጨረሻ ደቂቃ ስምምነት ካልተደረሰ በስተቀር፤ ችሎቱ ዛሬ ስምንት ከሕዝብ የተወጣጡ ዳኞችን (ጁሪ) በመምረጥ ይጀምራል ተብሏል።
ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መጋቢት 1፣ 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር ቢሾፍቱ አካባቢ ተከስክሶ በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ ሁሉም 157 ተሳፋሪዎች መሞታቸው ይታወቃል።
@sputnik_ethiopia