ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ዓመታት ዓለማቀፍ የልማት ግቦችን በጥሩ ደረጃ እያሳካች እንደሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ
11:28 07.04.2025 (የተሻሻለ: 11:44 07.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ ባለፉት 6 ዓመታት ዓለማቀፍ የልማት ግቦችን በጥሩ ደረጃ እያሳካች እንደሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ዓመታት ዓለማቀፍ የልማት ግቦችን በጥሩ ደረጃ እያሳካች እንደሆነ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ
አፈ ጉባኤው ኡዝቤኪስታን በሚካሄደው 150ኛ ዓለማቀፍ የፓርላማ ሕብረት ጉባኤ ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ነው፡፡
አፈ ጉባኤው አገኘሁ ተሻገር በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች እና ከአፍሪካ አጀንዳ 2063 ጋር የተጣጣመ የአሥር ዓመት ሀገራዊ የልማት ዕቅድ አውጥታ እየሠራች እንደምትገኝ አብራርተዋል። ባለፉት ስድስት ዓመታት ዓለም አቀፍ የልማት ግቦችን በማሳካት ረገድ ከፍተኛ ውጤት እያሳየች እንዲሁም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች እንደሆነም በንግግራቸው ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፓርላማ የሚሊኒየሙን የዘላቂ ልማት ግቦች ለማሳካት የተለያዩ ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞችና የሕግ ማዕቀፎችን መርምሮ በማፅደቅ፣ ክትትልና ድግፍ በማድረግ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል ማለታቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታውቋል፡፡
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
