የቶጎ ፕሬዝዳንት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት ዙሪያ የሚካሄደውን ሽምግልና እንዲመሩ በአፍሪካ ሕብረት ተመረጡ
19:01 06.04.2025 (የተሻሻለ: 19:24 06.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቶጎ ፕሬዝዳንት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት ዙሪያ የሚካሄደውን ሽምግልና እንዲመሩ በአፍሪካ ሕብረት ተመረጡ
የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ጃኦ ሎሬንሶ የቶጎ ፕሬዝዳንት ፋር ግናሲንግቤ ሹመቱን እንደተቀበሉ ተናግረዋል።
የአፍሪካ ሕብረት ኃላፊነታቸው ላይ ትኩረት ለማድረግ ከአሸማጋይነታቸው በቅርቡ ያገለሉት ሎሬንሶ፤ በምስራቅ ኮንጎ እየተባባሰ የመጣው የሰብዓዊ ቀውስ አሳሳቢና ለቀጣናው መረጋጋት ስጋት ነው ብለዋል።
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሞሐመድ አሊ ዩሱፍ የሰላም ድርድሩ ፍኖተ ካርታ በጥልቅ መታየት አለበት ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።
የግናሲንግቤ ሹመት ከፀደቀ በኋላ በደቡብ አፍሪካ የልማት ማሕበረሰብ እና በምስራቅ አፍሪካ ማሕበረሰብ ከሚመረጡ አምስት አስተባባሪዎች ጋር በጋራ እንደሚሠሩ ተገልጿል።
@sputnik_ethiopia