ሩሲያ የሳህል ሕብረትን በግብርናው ዘርፍ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን የቡርኪናፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ
18:07 05.04.2025 (የተሻሻለ: 18:34 05.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ የሳህል ሕብረትን በግብርናው ዘርፍ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን የቡርኪናፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ የሳህል ሕብረትን በግብርናው ዘርፍ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን የቡርኪናፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ
የኮንፌዴሬሽኑ አላማ የሩሲያ እገዛ ሶስቱ ሀገራት ካሉበት የሰብዓዊ ቀውስ መውጣት እንዲችሉ ማረጋገጥ ነው ሲሉ ካራሞኮ ትራኦሬ ለስፑትኒክ ተናገረዋል።
የሳህል የምግብ ቀውስ ሃሙስ እለት በሩሲያ እና የሳህል ሀገራት ጥምረት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መካከል በተደረገው ውይይት ወቅት አንዱ አጀንዳ እንደነበር ሚኒስትሩ አክለዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ ግቡን ለማሳካት የሚከተሉት እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው፦
🟠 ውጤታማ እርምጃዎችን መተግበር፣
🟠 የማዳበሪያ አቅርቦትን ማረጋገጥ፣
🟠 ከግብርና ሎጂስቲክስ አንፃር አስፈላጊውን እርምጃ ተግባራዊ ማድረግ።
ትራኦሬ በቡርኪናፋሶ የስንዴ ማሳዎች ዙሪያ የትብብር አቅም እንዳለ በመግለፅ፤ የሩሲያ የተረጋገጠ የግብርና እውቀት ለሳህል ሀገራት ጠቃሚ እንደሚሆን ተናግረዋል።
@sputnik_ethiopia