የ2024 የኢትዮጵያና ኡጋንዳ የንግድ ልውውጥ 5.46 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየ2024 የኢትዮጵያና ኡጋንዳ የንግድ ልውውጥ 5
የ2024 የኢትዮጵያና ኡጋንዳ የንግድ ልውውጥ 5 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 05.04.2025
ሰብስክራይብ
የ2024 የኢትዮጵያና ኡጋንዳ የንግድ ልውውጥ 5.46 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር ተገለፀ

ይህ የተገለፀው በአራተኛው የኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ነው።

በስብሰባው የኢትዮጵያ የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ከኡጋንዳ አቻቸው ፍራንሲስ ምቤሳ ጋር የንግድ ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ነባር ወዳጅነት የሚያጠናክርና የንግድ ትብብር ማዕቀፍን ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የንግድ ፕሮሞሽን፣ የንግድ መረጃና ቴክኒክ ልውውጥ አንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ትሥሥርን ከማሳለጥ አንጻር በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ እንደደረሱ ታውቋል።

@sputnik_ethiopia

መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የ2024 የኢትዮጵያና ኡጋንዳ የንግድ ልውውጥ 5 - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የ2024 የኢትዮጵያና ኡጋንዳ የንግድ ልውውጥ 5 - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0