የአማራ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ ተጀመረ
12:14 05.04.2025 (የተሻሻለ: 12:34 05.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአማራ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ ተጀመረ
በክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር መካሄድ የጀመረው አጀንዳ የማሰባሰብ ፕሮግራም ከተለያዩ ክፍሎች የተወጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የሚያሳትፍ እንደሆነ ተነግሯል።
የወረዳ ማሕበረሰብ ክፍል ወኪሎችን ጨምሮ የመንግሥት፣ የተቋማትና ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች አጀንዳቸውን እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
ከዛሬ እስከ ሚያዚያ 4 ድረስ በሚቆየው የአማራ ክልል የምክክር መድረክ በጥቅሉ ከ6 ሺህ በላይ ወኪሎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
በአማራ ክልል ምክክር ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ በመኖሩ ሥራውን ለማከናወን እንደተወሰነ የኢትዮጵያ ምክክር ኮሚሽን ትናንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ