ኢትዮጵያ የ70 ሚሊየን ዶላር የካርበን ሽያጭ ስምምነት ተፈራረመች
11:58 05.04.2025 (የተሻሻለ: 12:14 05.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የ70 ሚሊየን ዶላር የካርበን ሽያጭ ስምምነት ተፈራረመች
ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ስምምነቱን እንደተፈራረመች የኢትዮጵያ ደን ልማት አስታውቋል። የሀገር ውስጥ ሚዲያ ስምምነቱ ዓለም ባንክ እና የኖሮዌይን መንግሥት እንደሚያካትት ዘግቧል።
የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ወደ 23.6 በመቶ እንዳደገ መረጃዎች ያሳያሉ።
በ2024 ሞስኮ በተካሄደው የብሪክስ የአየር ንብረት መድረክ የብሪክስ የጋራ የካርበን ገበያ የማቋቋም እቅድ መቅረቡ የሚታወስ ነው።
@sputnik_ethiopia