የኢትዮጵያ አበዳሪዎች የሀገሪቱን የዕዳ መክፈያ ጊዜ አራዘሙ
21:52 04.04.2025 (የተሻሻለ: 22:24 04.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አበዳሪዎች የሀገሪቱን የዕዳ መክፈያ ጊዜ አራዘሙ
የኢትዮጵያ ይፋዊ አበዳሪዎች የዕዳ ሽግሽጉን በአንድ ወር ውስጥ ያጠናቅቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የምዕራባውያኑ ሚዲያ ዘግቧል።
ስምምነቱ ግን የዕዳ ቅነሳን እንደማያካትት አበዳሪዎቹ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር 8.4 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ዕዳዋን ለማሸጋሸግ ስምምነት ላይ እንደደረሰች በቅርቡ ማስታወቋ የሚታወስ ነው።
ሀገሪቱ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ፕሮግራም ሥር ከነበሩ ሀገራት አንጻር በአበዳሪዎች የመክፈል አቅሟ የተሻለ ነው የሚል ግምት እንደተሰጣት ዘገባው ጠቁሟል።
@sputnik_ethiopia