ኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞችን የጡረታ ተከፋይ የሚያደርግ ሕግ ልታፀድቅ ነው
15:02 04.04.2025 (የተሻሻለ: 15:24 04.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞችን የጡረታ ተከፋይ የሚያደርግ ሕግ ልታፀድቅ ነው
ደንቡ የቤት ሠራተኞችን የማሕበራዊ አግልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው። በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ደንቡ በዋናነት ወጥ እና ሕጋዊ ተቀባይነት ያለው እና ሠራተኛውን እና አሠሪውን ተጠቃሚ የሚያደርግ ውል የመፍጠር ዓላማ አለው።
ደንቡ ሥራ ላይ ሲውል የቤት ሠራተኞች የሕክምና አገልግሎት እና ጡረታን ጨምር የማሕበራዊ ዋስትና ጥቅሞችን እንዲያገኙ የሚፈቅድ እንደሆነ ተነግሯል።
@sputnik_ethiopia