ቢዋይዲ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ምርት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበለት
13:35 04.04.2025 (የተሻሻለ: 13:54 04.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቢዋይዲ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ምርት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበለት

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቢዋይዲ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ምርት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበለት
የቢዋይዲ (BYD) ኤሌክትሪክ መኪና ዲዛይን ባለቤት የሆነው የቻይናው ሻንጋይ ላውንች አውቶሞቲቭ ኩባንያ ኃላፊዎች ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ የባትሪ ምርት ጥሬ ዕቃ ማዕድን እንዳላት የተነሳ ሲሆን ኩባንያው ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ቢጀምር ትርፋማ እንደሚሆን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች ተናግረዋል።
ኩባንያው በታዳሽ ኃይል ዘርፍ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች የዲዛይን አገልግሎትን ጨምሮ የምርምርና ልማት ማዕከልን በማቋቋም ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚፈልግ መግለጹን ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
@sputnik_ethiopia