የሩሲያ ልዩ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪዬቭ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በዋሽንግተን ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት አስተያየት የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
12:26 04.04.2025 (የተሻሻለ: 12:34 04.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ልዩ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪዬቭ ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በዋሽንግተን ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት አስተያየት የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ሩሲያ እና አሜሪካ ባለፉት ሁለት ቀናት ግንኙነታቸውን ሶስት እርምጃ ወደፊት መውሰድ ችለዋል።
በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ዙሪያ ወሳኝ ለውጥ ታይቷል።
የተለያዩ አካላት በሞስኮ እና በዋሽንግተን መካከል የሚደረገውን ውይይት ለማደናቀፍ እየሞከሩ ነው።
ልዩነቶች ቢቀሩም ሁለቱም ወገኖች ችግሩን ለመፍታት እየሠሩ ነው።
የትራምፕ አስተዳደር የሩሲያን አቋምና ስጋት ተቀብሏል።
ሁሉንም አለመግባባቶች ለመፍታት ተጨማሪ ግኑኝነቶች አስፈላጊ ናቸው።
ንግግሩ የአርክቲክ እና ውድ የምድር ብረቶች ላይ የሚደርግ ትብብርን ያካተተ ነበር።
የአሜሪካ እና ሩሲያ አዲስ የውይይት ፕሮግራም በቅርቡ ይወሰናል።
ዲሚትሪዬቭ የአሜሪካ ባልደረቦቻቸው ሩሲያን እንዲጎበኙ ጋብዘዋል።