በሞስኮ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሩሲያ የንግድ ማሕበረሰብ በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር እንዲጠቀም ጋበዙ
11:47 04.04.2025 (የተሻሻለ: 12:04 04.04.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሞስኮ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሩሲያ የንግድ ማሕበረሰብ በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር እንዲጠቀም ጋበዙ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሞስኮ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሩሲያ የንግድ ማሕበረሰብ በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር እንዲጠቀም ጋበዙ
በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ የሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤትን በትላንትናው እለት ጎብኝተዋል፡፡ በዘህ ወቅት የሩሲያ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ኤምባሲው ከምክር ቤቱ ጋር በመተባበር የንግድ ትውውቅ መድረኮችን እንዲያዘጋጅ ጠይቀዋል፡፡
አምባሳደሩ በበኩላችው ኢትዮጵያ ቅድሚያ ስለምትሰጣቸው የንግድ ዘርፎች፣ በሀገሪቱ ስላለው ምቹ የኢንቨስትምንት ምህዳር እና መንግሥት ለውጭ ኢንቨስትሮች ስለሚሰጣቸው ማበረታቻዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት እና ሌሎች አመራሮች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ እና የንግድ እድሎችን እንዲቃኙ ማበረታታቸውን ሞስኮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
@sputnik_ethiopia
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
