የኢትዮጵያ ግብርና ሜካናይዜሽን ምርታማነትን በከፈተኛ ሁኔታ እያሳደገ እንደሆነ ተገለፀ
21:02 03.04.2025 (የተሻሻለ: 21:24 03.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ግብርና ሜካናይዜሽን ምርታማነትን በከፈተኛ ሁኔታ እያሳደገ እንደሆነ ተገለፀ
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ባለፈው የመኸር ወቅት ከታረሰው 20.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ 25 በመቶው በትራክተር መታረሱን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ የግብርና ሜካናይዜሽንን ለማስፋፋት መንግሥት የፖሊሲ እርምጃዎችን እንደወሰደም ጠቅሰዋል። ለአብነትም የእርሻ ማሽነሪዎች ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ለአርሶ አደሮች ተደራሽ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም የኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ግብዓትን በራስ አቅም በመሸፈን ለግብርናው ዘርፍ አዲስ የታሪክ እጥፋት ያመጣል ብለዋል ሲል የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በፓርላማ ቀርበው ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፤ መንግሥት ከውጭ የሚያስገባውን የአፈር ማዳበሪያ ለመተካት የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ማቀዱን ገልፀዋል።
@sputnik_ethiopia