ኢትዮጵያ የሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራን በ334 ወረዳዎች አስፋፋች
20:26 03.04.2025 (የተሻሻለ: 20:54 03.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራን በ334 ወረዳዎች አስፋፋች
የኢትዮጵያ የምግብ እና ስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን የሚኒስትሮች ስቲሪንግ ኮሚቴ የስድት ወር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፕሮግራሙን ተደራሽ ለማድረግ የመንግሥትና የአጋሮችን ድጋፍ በማስተባበር እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
በመድረኩ በሰቆጣ ቃልኪዳን የስድት ወር አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት እንደተደረገ የጤና ሚኒስቴር በማህበራዊ የትሥሥር ገፁ አስነብቧል።
በ2007 ዓ.ም የተፈረመው የሰቆጣ ቃልኪዳን ከሁለት ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ከመቀንጨር ለመከላከል ወጥኖ የተነሳ ነው። ቃልኪዳኑ ከ7.8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሕጻናትን በ15 ዓመት ውስጥ ከመቀንጨር ለመታደግ ያቀደ ነው።
@sputnik_ethiopia