የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለተመድ የዲጂታል እና አዲስ ቴክኖሎጂዎች አጋርነት ጠንካራ እጩ ነው ተባለ
13:51 03.04.2025 (የተሻሻለ: 14:14 03.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለተመድ የዲጂታል እና አዲስ ቴክኖሎጂዎች አጋርነት ጠንካራ እጩ ነው ተባለ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዲጂታል እና አዲስ ቴክኖሎጂዎች ቢሮ ረዳት ዋና ፀሐፊ አማንዲፕ ሲንግ ጊል የተመራ የልዑካን ቡድን ኢንስቲትዩቱ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ከኢትዮጵያ ልማት ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ በማዋሃድ እያስመዘገበ ያለውን ከፍተኛ እድገት አድንቀዋል።
ልዩ መልክተኛው ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ በሰው አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራቸው ላሉ ተግባራትም እውቅና ተሰጥተዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና ተቋሙ በተለያዩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መፍትሄውች ዙሪያ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ እንደሆነ ተናግረዋል።
@sputnik_ethiopia