ኢትዮጵያ ከ22 ቶን በላይ ወርቅ ለውጪ ገበያ አቀረበች
13:04 03.04.2025 (የተሻሻለ: 13:34 03.04.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከ22 ቶን በላይ ወርቅ ለውጪ ገበያ አቀረበች
የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኘ ባለፉት ስምንት ወራት ከ22 ቶን በላይ ወርቅ ለውጪ ገበያ መቅረቡን አስታውቀዋል።
ለውጪ ገበያ እየቀረበ ያለው የወርቅ ምርት አሁን ባለበት ሁኔታ ከቀጠለ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 33 ቶን ይደርሳል ብለዋል። ሚኒስትሩ አክለውም ወደ ውጭ ከተላከው የወርቅ ምርት 95 በመቶ የሚሆነው በባህላዊ መንገድ የተመረተ መሆኑን አስረድተዋል።
ከማዕድን ዘርፍ የወጪ ንግድ ከተገኘው 1.88 ቢሊዮን ዶላር የወርቅ ምርት ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ሚኒስትሩን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
@sputnik_ethiopia